ማስታወቂያ


 ለክቡራን ታካሚዎችና ቤተሰቦቻቸው
በሌቭ ሃሻሮን የአዕምሮ ጤና አገልግሎት ሆስፒታል ውስጥ በቀላሉ ለመስተዳደር የሚያስችላችሁን ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት ትችላላችሁ፡
ስለማንኛውም ክፍል መረጃ በሚመለከተው የክፍሉ ቢሮ ማግኘት ይቻላል
የቢሮ ስልክ ቁጥር: 09-8981111

የታካሚዎች ጉብኝት ስዓት፡
የህመምተኛ ቤተሰቦች በታካሚው ክፍል ውስጥና ከክፍሉ ውጪ ስለሚያደርጉት የጉብኝት ስዓትና ግዜ የህክምና ባለሙያዎችን ማሳወቅ ያስፈልጋል::
የጉብኝት ስዓት፡
ከቀኑ  15-00 (ሶስት ሰዓት) እስከ ምሽቱ 20-00 ስምንት ስዓት)
አርብ ቀን: ከጠዋቱ 11-00 (አስራ አንድ ሰዓት) እስከ ምሽቱ 20-00 ስምንት
ቅዳሜና በበዓላት ቀን : ከጥዋቱ 10-00 (አስር ስዓት) እስከ ምሽቱ 21-00 (ዘጠኝ ስዓት)

ሲጋራ ማጨስ

በህመምተኞች ክፍል ውስጥና በሆስፒታሉ ውስጥ ሲጋራ ማጨስ በጥብቅ የተከለከለ ነው: በሆስፒታሉ የአጥር ግቢ ውስጥ ሲጋራ ማጨስ ይፈቀዳል::

አልባሳት
ለህመምተኞች አገልግሎት የሚውል ሆስፒታሉ የሚሰጠው ልብስ ቢኖርም በታካሚውና ቤተሠቦቹ ፍላጎትና ሓላፊነት በግል ልብስ መጠቀምም ይቻላል: ለህመምተኛው የግል አገልግሎት የሚሆኑ ዕቃዎችን በምታመጡበት ግዜ ለሆስፒታሉ የህክምና ባለሙያዎች ወይም የክፍል ሀላፊዎች ማሳወቅ ያስፈልግስል::

የንጽህና አጠባበቅ
ስለት ያላቸው እንደ መቀስ እና የጺም ምላጭ አይነት ዕቃዎችን ሆስፒታሉ ውስጥ ማስገባት በህግ የተከለከለ ነው፡:

ውድ ዋጋ ያላቸው እቃዎች
የከበረ ዋጋ ያላቸውን የግል ዕቃዎች ወይም ህመምተኛው ለሚጠቀምባቸው ዕቃዎች ደህንነት ሆስፒታሉ ሀላፊነትን አይወስድም፡

ለማንኛውም ታካሚ አገልግሎት የሚውል የቁም ሣጥን ከቁልፍ ጋር ይሰጣል፡
ገንዘብና የከበረ ዋጋ ያላቸውን የታካሚው ንብረቶች ሆስፒታሉ ውስጥ በሚገኘው ልዩ የመጠበቂያ ሣጥን መጠቀም ይቻላል፡ ነገር ግን ታካሚው ሆስፒታሉን ለቆ በሚወጣበት ግዜ ንብረቱን ማስመለስ አለበት፡
ህመምተኛው ለሚጠቀምባቸው የዕለት ተዕለት የግል ዕቃዎች ሆስፒታሉ ሀላፊነት አይኖረውም፡
በሆስፒታሉ ልዩ መጠበቂያ ሣጥን ላልተያዙ ወይም ላልተጠበቁ የታካሚው የግል ዕቃዎች ሀላፊነቱን አይወስድም፡
በየክፍሉ የመረጃ ሠሌዳ ወይም ወረቀት ላይ ስለ መድሃኒት አጠቃቀም ስለሆስፒታሉ የአገልግሎት ጥራትና የታካሚዎች ህጋዊ መብቶችን የያዘ መረጃ ያገኛሉ።

የመዝናኛ ክፍል(ካፍቴሪያ)
የመዝናኛው ክፍል (ካፍቴሪያ) ለታካሚዎችና ለቤተሰቦቻቸው በቀጣይነት በተገለጹት ሠዓታት ክፍት ሆኖ አገልግሎት ይሰጣል፡
ከእሁድ እስከ ሐሙስ ባሉት ቀናት
ከጠዋቱ 10፡30 (አስር ሠዓት ተኩል) እስከ
ምሽቱ 19፡00 (ሠባት ሠዓት)
አርብ ቀን ከጠዋቱ 10፡00 (አስር ሠዓት) እስከ ቀኑ 13፡30 (አንድ ሠዓት ተኩል)
ከመዝናኛው ክፍል እና ከክልኒኩ አጠገብ የሚገኙ የቀላል መጠጥና የቀላል ምግቦች የሚገዛበት ማሽን ለማንኛውም ሠው በማንኛውም ሠዓት አገልግሎት ይሠጣል።

ሆስፒታል የመልቀቂያ ግዜ
ታካሚው ሆስፒታሉን በሚለቅበት ግዜ ቀጣይ ህክምናውን በተመላላሽነት ከመደበኛው ሀኪም ወይም በሚኖርበት አካባቢ በሚገኝ ክልኒክ የቤተሠብ ሀኪም አማካኝነት መከታተል ይችላል።
ታካሚው በሚለቅበት ግዜ በተኛበት ክፍል የህክምና ባለሙያዎች ሀላፊነት የመድሃኒት አጠቃቀም ገለፃ ይደረግለታል።

ማሳሰቢያ
መድሃኒቶችን ወይም ሌሎች የህክምና መገልገያዎችን ለማግኘትና የአጠቃቀም ገለፃ ለማግኘት እንዲሁም የቀጠሮ ቀን ለመውሰን ለወ/ሮ  ሪቭቃ ለቪ በስልክ ቁጥር 09-8981207 ደውሎ መረጃ ማግኘት ይቻላል።
ለታካሚዎች መልካም ምህረትን እየተመኘን ከላይ በተገለፀው መመሪያ መሠረት በአንድነትና በስምምነት አብረን መስራት እንደምንችል ተስፋ እናደርጋለን።
ለተጨማሪ መረጃ ከህክምና ባለሙያዎች ዘንድ መጠየቅ ይቻላል።

በአክብሮት
የህክምና ባለሙያዎችና የሆስፒሉ፡ አስተዳደር።